Tikikil Neh Lyrics
- Genre:Gospel
- Year of Release:2023
Lyrics
እንደዚ እና እንደዚያ አትባልም
በገዛ ፍጥረትህ አትመረመርም
የምታደርገውን ጠንቅቀህ ታውቃለህ
እግዚአብሄር አንተ እንደ ሰው አይደለህ
የፊት የኋላውን የምታይ አምላክ ነህ
አንተ አትሳሳትም ስትፈርድም ልክ ነህ
ብቻህን ቅን ዳኛ ማንም አይመስልህም
በስራህ ጻድቅ ነህ በሰማይ በምድርም
አንተ እጅግ ትልቅ ነህ
ሁሉን ታውቃለህ
ትክክል ነህ ኦሆሆ ትክክል ነህ
ትክክል ነህ የኔ ጌታ ትክክል ነህ
አንተ እጅግ ትልቅ ነህ
ሁሉን ታውቃለህ
ትክክል ነህ ኦሆሆ ትክክል ነህ
ትክክል ነህ የኔ ጌታ ትክክል ነህ
ያን ታናሽ እረኛ መርጠህ ስትቀባው
መች በኩር ነበረ ለስራህ ስትጠራው
በሰው አይን ማይሞላ ደካማ የተባለ
ቁመትና ጉልበት መስፈርትህ አልነበረ
ያለ አማካሪ እራስህን ታምነህ
እንደ ልብህ ሆነ ክብርህን በእርሱ ገለጠህ
አደራረግህ ላይ ሁልጊዜ ፍፁም ነህ
ከቶ አትሳሳትም አንተ እግዚአብሄር ነህ
አንተ እጅግ ትልቅ ነህ
ሁሉን ታውቃለህ
ትክክል ነህ ኦሆሆ ትክክል ነህ
ትክክል ነህ የኔ ጌታ ትክክል ነህ
አንተ እጅግ ትልቅ ነህ
ሁሉን ታውቃለህ
ትክክል ነህ ኦሆሆ ትክክል ነህ
ትክክል ነህ የኔ ጌታ ትክክል ነህ
ባይገባኝም እንኳን አንዳንዴ ማልፍበት
ዘመናት ይመስክር ያንተን አዋቂነት
በምድረበዳ ላይ ከአለት ምንጭ አፍልቀህ
ማኖር የምትችል ኤልሻዳይ አምላክ ነህ
ፍጥረትም ይናገር ከልካይ እንደሌለህ
በአፍህ ቃል ብቻ ሁሉን ታጸናለህ
በዙፋንህ ሆነህ ሁሉንም ታያለህ
አንተ ግን መሪ ነህ በማን ትመራለህ
አንተ እጅግ ትልቅ ነህ
ሁሉን ታውቃለህ
ትክክል ነህ ኦሆሆ ትክክል ነህ
ትክክል ነህ የኔ ጌታ ትክክል ነህ
አንተ እጅግ ትልቅ ነህ
ሁሉን ታውቃለህ
ትክክል ነህ ኦሆሆ ትክክል ነህ
ትክክል ነህ የኔ ጌታ ትክክል ነህ