Adinonal Lyrics
- Genre:Gospel
- Year of Release:2023
Lyrics
የምን እዳ እዳችን ተከፍሏል
በመስቀል ላይ ኢየሱስ ተሰቅሏል
ሞተ ሲሉት ፈንቅሎ ተነስቷል
አድኖናል አድኖናል /2/
ደም ተከፍሎ ከእግዚአብሄር ጋር ተታርቀናል
ትንሳኤና ህይወት ኢየሱስ ሆኖልናል
ህያው ተስፋን ተቀብለን በታላቅ ምህረቱ
በአዲስ ልደት ልጆች ሆንን ህይወት ሆኖን ሞቱ
በመንፈስ ቅዱስም አትሞናል
አሮጌውን ህይወት አስንቆናል
ታዲያ አዳኛችን ብለን ስንለው
ያደረገልን ገብቶን እኮ ነው
የምን እዳ እዳችን ተከፍሏል
በመስቀል ላይ ኢየሱስ ተሰቅሏል
ሞተ ሲሉት ፈንቅሎ ተነስቷል
አድኖናል አድኖናል /2/
በዚህ የለም ህያው ሆኖ መቃብር ፈንቅሏል
ሞትን ድል ነስቶ እግዚአብሄር ወልድ በክብር አርጓል
ያለ የነበረው በአብ ቀኝ ያለው የዘላለም ጌታ
ያዩታል የወጉት ከደመና ጋር ዳግመኛ ሲመጣ
የእግዚአብሄር በግ ለኛ የታረደው
ከሞት ማምለጫ እርሱ ብቻ ነው
ያለም መድኃሊት ዛሬም የሚያድነው
ብቻውን ክብር የተገባው ነው
አሜን አሜን ክብር ይሁንለት ክብር ይሁንለት/2/