![Hiyawu Meswaet](https://source.boomplaymusic.com/group10/M00/05/24/1a2779297497417ca66073d8f20730e4_464_464.jpg)
Hiyawu Meswaet Lyrics
- Genre:Gospel
- Year of Release:2023
Lyrics
ያለኝን የሰጠኸኝን መልሼ እሰዋዋለው
አምልኮዬን ዝማሪዬን አምላኬ ይኸው ተቀበለው
ካንተ ነው እና ላንተ ነው /4/
ቅኔዬን ይኸው አምልኮዬን ይኸው
ህይወቴን ይኸው ማንነቴን ይኸው
አንዳች የለኝም ከኔ ነው የምለው
ሰጭው አንተው ነህና ስለዚህ ይኸው
ህያው መስዋዕት አድርጊ ካልከኝ
ብዙ አምልኮ ክብር ላንተ አለኝ
ለአምላኬ ተሰብሮ የተዋረደን ልብ
ይኸው ጌታዬ ሆይ በፊትህ ላቅርብ
የምቀበለው ያን ነው
እኔ የምወደው ያን ነው
ብለህ በቃልህ እንዳልከው
ዘመኔን ሁሉ ይኸው ውሰደው
የምቀበለው ያን ነው
እኔ የምወደው ያን ነው
ብለህ በቃልህ እንዳልከው
ዘመኔን ሁሉ ይኸው ውሰደው
የነፍስ መስዋዕት ከሁሉም የሚበልጥ
ተሰቶኝ የለ ወይ በቃል የማይገለጥ
የእስትንፋሴስ ምንጭ አንተ አይደለህ ወይ
ብሰዋልህ ሁሉን እጅግ አያንስህም ወይ
ህያው መስዋዕት አድርጊ ካልከኝ
ብዙ አምልኮ ክብር ላንተ አለኝ
ለአምላኬ ተሰብሮ የተዋረደን ልብ
ይኸው ጌታዬ ሆይ በፊትህ ላቅርብ
የምቀበለው ያን ነው
እኔ የምወደው ያን ነው
ብለህ በቃልህ እንዳልከው
ዘመኔን ሁሉ ይኸው ውሰደው
የምቀበለው ያን ነው
እኔ የምወደው ያን ነው
ብለህ በቃልህ እንዳልከው
ዘመኔን ሁሉ ይኸው ውሰደው