እንደው ይገርማል/Endew Yigermal Lyrics
- Genre:Alternative
- Year of Release:2023
Lyrics
እንደው ይገርማል ቀን ከፍቷል ዘንድሮ
እንደው ይገርማል ገንዘብ ከ ሰው ከብሮ
እንደው ይገርማል ቀን ከፍቷል ዘንድሮ
እንደው ይገርማል ገንዘብ ከ ሰው ከብሮ
እንደው ይገርማል ቀን ቀን ወልዶ ሰው ከፍቷል
ወንድሜ ያልኩት አብሮኝ የለም ከጎኔ እንኳ ቆሞ
ያኔ ለሃገር ለምድሩ የወንድሜ የጓድ ውብ ምሳሌ
እኔ እና አንተ ስንኖር በፍቅር ቅጥር ድንበር ሳይኖረን
እንኳን እኔ እና አንተ ለ ስንቱ ምስኪን ተርፈን
ዘንድሮ መሯል ያጠዋት ማለዳ መሳይ ፍቅራችን
ጠውልጋ ፅጌሬዳዋ መልሳ አብባ ላትታይ
ወይኔ ጉዴ አንዴም እንኳን ቁጭ ብለን ሳንወያይ
ወንድሜ ወንድሜ ክብብሮሽ ቀርቶ ድብብቆሽ ሰፍቶ
እሱ ይሄ ሆኖ ስማችን ጥላቻ ሞት መለያችን
አይ ሲያምር መነሻችን ሲያሳዝን ግን መድረሻችን
ያኔ በፍቅር እንዳልኖርን
አሁን ግን አውሮን
ቀን ወልዶ ከፋብን እና
ወጣን ለጦር እንደገና
እንደው ይገርማል ቀን ከፍቷል ዘንድሮ
እንደው ይገርማል ገንዘብ ከ ሰው ከብሮ
እንደው ይገርማል ቀን ከፍቷል ዘንድሮ
እንደው ይገርማል ገንዘብ ከ ሰው ከብሮ
ከዘፍጥረት መሰረት የሰው ልብ እርሻ ማዕረጉ
የሰጡትን የዘር ፍሬ አብቅሎ ተክል ማድረጉ
ያኔም አብረን አቻ ለ አቻ ከክፋት አባም ይፍታ ሲሉ
ሃጂም እስላም ሰላም ብለው ስለ ፍቅር ሲመርቁ
ዛሬ ምነው መራቁ ከልባችን መልክቱ የአምላክ
ሰው እና ሰው አብሮ እንጂ ቃኤል ከ አቤል አይወድ አምላክ
ከቶ እንዴት ሊረዳው ቢሰናከል አንዱ በሌላ
በሉ አብረን እንብላ እንደለመድነው በአበው ስርዐት
መሶብ እንኳን እነ እማ ሲሰፉት ክብ ነው እና
ጥላቻን ተዋጋ በሁሉ አንጻር በህብረት መላ አለ እና
ልብህን ጠብቅ ንቃ እና ዘመኑ ተሻግሯል እና
ወንድምህን ውደደው በል ሲመሽ ይራዳል እና
የሃገርህ ልጅ ጀግና እኮ ነው ጃል ዝናው ውቅያኖስ ሰባሪ
አንተም ሁን የ ጥቁር አንበሳ አደራን አክባሪ
ድል ብስራት አብሳሪ የሰላም ዘብ ለወንድሙ
ወራሪን ወራሪ የጥቁሩ ሰውዬ ልጅ መራራው ደሙ
ከንዋይ ፍቅር ነው ሃብቱ ንገረው ለውስጥህ እውነቱን
ይብቃ ውዝግብ ውሸቱ ስንዴ ዘርቶ ጤፍ ሙሉ ማጀቱ
የአንበሳ ልጅ ጅብ ላይሆን ልዩነቱ ነው ውድቀቱ
የአንበሳ ልጅ ጅብ ላይሆን ልዩነቱ ነው ውድቀቱ
እንደው ይገርማል ቀን ከፍቷል ዘንድሮ
እንደው ይገርማል ገንዘብ ከ ሰው ከብሮ
እንደው ይገርማል ቀን ከፍቷል ዘንድሮ
እንደው ይገርማል ገንዘብ ከ ሰው ከብሮ